Posts

Showing posts from February, 2021

አትሙቺብኝ እማ

Image
ሙቺብኝ እማ═               ═══❁✿❁ ════   አትሙቺብኝ እማ  ልሙትልሽ እኔ ወገን እና ዘመድ የለኝም ከ ጎኔ ክፉሽን አልየው በ አጭሯ ዘመኔ ያላንቺማ እናቴ ህይወቴ ባዶ ነው የለኝም ጓደኛ የእኔ ነው የምለው ባክሽ አትሙቺብኝ ኑሪልኝ ዘላለም እኔነቴን የሚያውቅ ከ አንቺ ሌላ የለም ጊዜ የማይሽረው የሚኖር ዘላለም ፍቅርሽን ሚተካ በ አለም ላይም የለም          ¤ እናልሽ እማዬ ¤ ያላንቺ አልኖርም እኔማ ባዶ ነኝ እኔም እኔ አይደለሁ እማ ያንቺ እኮ ነኝ  ስጠራሽ ተነሺ  እቅፍ አድርገሽ  ሳላለቅስ አባቢይኝ እኔ ልውደቅልሽ አንቺማ አትከፊ ይህን ክፉ ዘመን አብረሽኝ እለፊ

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
       💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                  #ክፍል_3 ...🖌በክፍል ሁለት እንደምታስታውሱት መቅደስና ዮናስ ካፌ ቁጭ ብለው እያወሩ ሳለ ነበር ጌዲዮ ባጋጣሚ መጥቶ አይን ላይን የተፋጠጡት.... .......መቅደስ ከመቀመጫዋ ተነሳች ጌዲዮም በነበረበት ቆሞ እሷን እያየ ጭንቅላቱን ያዘ መቅደስ በድንጋጤ ሙክክ ብላለች እንደው አይተው ሲገምቷት ባሏ ከሌላ ወንድ ጋር የያዛትን ሴት ነው የምትመስለው ጌዲዮ ሰውነቱን እንደማንቀጥቀጥ አደረገው ይህን ጊዜ ሊያመው እንደሆነ አወቀች መቼም መቅደስ የግቢው ቅፅል ስሟ የጌዲዮ የግል ነርስ ሆኗል በፍጥነት እየተንቀጠቀጠች ቦርሳዋን ከፈተች..... ዮናስ ምንም እንዳልተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው እንኳን አላላትም ምክንያቱም ጌድዮን አይቶታል መቅደስም ቦርሳዋን ጠረንቤዛው ላይ ዘረገፈችው ይህን ጊዜ ዮናስ ብዙ ሴቶች ወደሱ እያዩ ስለነበር ሼም ያዘው ለመነሳትም አቃጣው መቅደስም በሚርበተበተው አንደበቷ ማማማ ማን ነበር ያያያ..ልከኝ...አ..ው..ዮ.ናስ.እእ..ባክህ..ክርቢት..ካካ..ለህ ይዤ ነነ.በር እ..ኮ.ጠፍኝ አለችው ዮናስም ከቦርሳዋ ከዘረገፈችው እቃ ወደ ክርቢቱ እያመለከተ ያውልሽ አላት መቅደስም ክርቢቱን ልታነሳ ስትቸኩል የብርጭቆውን ጁስ ዮናስ ላይ ደፋችበት ዮናስ በጣም ጮኸ ግን አልሰማችውም ይቅርታም ሳትለው ክርቢቱን ይዛ ወደ ጌዲዮ በረረች........ ......ከዛም ህመሙ ሳይብስበት ክርቢቱን አጫጭሳ ሰውነቱን አረጋግታ ደግፋ ከወንዶች ማደሪያ በር ላይ አድርሳው ተመለሰች ስትመለስ ዮናስም ወደማደሪያው እየሄደ ተገጣጠሙ ከዛም በጣም ይቅርታ አለችው በርግጥ በሰአቱ ስትደፋበት ብዙ ሴቶች ቢስቁም የለበሰውን...

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
 ​​​​​​​​.               💓❦የአሳዛኝ የፍቅር ታ                        #ክፍል_2 ...🖌መቅደስ ድንጋጤው ባይለቃትም አቅሟን ሰብስባ ጌድዮን ወደ ወደቀበት ስፍራ በረረች ነገር ግን በጣም እየተወራጨ ስለነበር የምታደርገው ጠፋት ከዛም አያቷ ለሚጥል በሽታ የክርቢት ጭስ ጥሩ እንደሆነ ያወሩት ትዝ አላትና ሁሉም ተማሪ ጋር እየዞረች ክብሪት ያለው ማለት ጀመረች።በሁኔታዋ እሩቅ የነበሩት ሁሉ መሰባሰብ ጀመሩ አብሮ አበድ ሳትባልም አይቀር መቅደስ በዛ ሰአት የስሟ ነገር ግድም አይሰጣትም ግን አለኝ እንቺ የሚላት አጣች ውስጥ ውስጡን ይስቁባት ይሳለቁባት ጀመር ። ከሰው እያደርኩኝ ሰው እንዴት ይናፍቀኝ ከሰው እያደርኩኝ ብርዱ እንዴት ተሰማኝ: አረ ጨከኑብኝ ተደፍቼ እያዩኝ ባላየ ባልሰማ ዝም ብለው አለፉኝ: የማን ያለህ ልበል ከንባ ጎርፍ በቀር ሰው በሰውነቱ ሲቀር ሳይከበር???? .......መቅደስ አለቀሰች እንደምንም ብላ ጭንቅላቱን ጭኖቿ ላይ አድርጋ ባፍና ባፍንጫው የሚፈልቀውን አረፋ በለበሰችው ነጠላ ትጠርግለት ጀመር አጭር ለማይባሉ ደቂቃዎች ማንቀጥቀጡ አላቆመም ነበር ከዛም ሊነቃ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሁሉም ተበተነ መቅደስ ግን አይኖቿን ከፊቱ ላይ ተክላ መንቃቱን ትጠባበቅ ጀመር። .......ከደቂቃዎችም ቡሀላ ጌድዮ አይኖቹ ከመቅደስ አይኖች ጋር ተጋጭተው ተገለጡ የመቅደስ አይኖች ማልቀሷን ያሳብቃሉ ከንፈሮቿም ይንቀጠቀጣሉ ጉንጮቿ በንባ እርሰው ላይን ያሳሳሉ ጌዲዮ ትኩር ብሎ አያት እሷም ከመደንገጧ የተነሳ ሰውነቷን መቆጣጠር ከበዳት። ጌዲዮ ቀስ ብሎ ከግሮቿ ላይ ተነሳ አስተያየቱ...

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
 ​​​​​​​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_1 ...🖌ዛሬ ቀኑ አዲስ ነው አሮጌ አመት አልቆ ሁሉም አዲስ ሆኗል ትምህርት ቤቶችም እየተከፈቱ ነው። ዩንቨርስቲዎችም ለተማሪዎቻቸው አቀባበል እያደረጉ ነው። ጌዲዮ የሁለተኛ አመት አመት የዲግሪ ተማሪ ነው። በባለፈው አመት አገር አቀፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጣውም እሱ ነው.....ዛሬ የሁለተኛ አመቱን ትምርት ሊቀጥል ሻንጣውን ሸክፎ የጅማ ዩኒቨርሲቲን እረግጧል።እናም አቀርቅሮ በመንገድ ላይ ሳለ አንዲት ቅልብልብ ያለች ቆንጆ ፊትለፊቱ መጥታ ተጋጩ ከዚያም እያየህ አትሄድም ብላ ጮኸችበት እሱ ግን ምንም ሳይላት መንገዱን ቀጠለ ልጅቱም ይቅርትታ ባለመጠየቁ ተናዳ ተከትላ ሄዳ ልብሱን ያዘችና እያናገርኩህ አይደል አለችው ያምሀል አታስተውልም እያለች....የስድብ አይነት ታወርድበት ጀመር ጌዲዮን ግን እንኳን ይቅርታ ሊጠይቃት ቀናም አላለላት...... ብዙ ተማሪዎች ከሩቅ ሆነው በፍርሀት ነበር የሚያዩዋቸው ምክንያቱም ጌዲዮ ከባድ የሚጥል በሽታ አለበት ጊቢውን ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ከመፅሀፍና ደብተሩ ውጪ ጓደኛው ነኝ የሚል ማንም የለም ሲበዛ ኮስታራ ዝምተኛ። ብቸኛ ነው ከትምህርቱ ውጪ ከመምህራኖቹ ጋር እንኳን አፍ ለአፍ ገጥሞ አያውቅም ማንም ሲስቅ አይቼዋለሁ የሚል የለም ከላይ ጀምሮ እስከታች ሁሉም ይፈሩታል። መቅደስ ግን አታውቀውም የመጀመሪያ አመት ትምህርቷን ለመከታተል ገና ጊቢውን መርገጧ ነው!!! .........

ውዴ

 ═══❁🌺✿🌺❁ ══════ እቅር ብዬሸለው ══════❁✿❁ ══════  ያለ ምንም ጥፋት ይቅርታ ጠየቅሽኝ ግፍ ሳትፈፅሚብኝ በፍቅር አሸነፍሽኝ በክህደት ቃሌ  ሰጠሽኝ ምሳሌ በቃ ተሸነፍሁኝ እጄንም አነሳሁ  ይቅርታሽ ማረኸኝ እኔነቴን አጣሁ በደሌ ሳያንስሽ በእምነትሽ ተቀጣሁ ይቅር በይኝ እህቴ ለሰራሁት ጥፋት ፍቅርሽን ገፍቼ ለሄድሁባት ሰአት በጣም ፀፅቶኛል ጥፋቴን ላርማት ያችን ቀን ላልደግማት ይቅሮታሽን ስጭኝ ሀቁን ልናገራት