አትሙቺብኝ እማ
ሙቺብኝ እማ═
═══❁✿❁ ════
አትሙቺብኝ እማ ልሙትልሽ እኔ
ወገን እና ዘመድ የለኝም ከ ጎኔ
ክፉሽን አልየው በ አጭሯ ዘመኔ
ያላንቺማ እናቴ ህይወቴ ባዶ ነው
የለኝም ጓደኛ የእኔ ነው የምለው
ባክሽ አትሙቺብኝ ኑሪልኝ ዘላለም
እኔነቴን የሚያውቅ ከ አንቺ ሌላ የለም
ጊዜ የማይሽረው የሚኖር ዘላለም
ፍቅርሽን ሚተካ በ አለም ላይም የለም
¤ እናልሽ እማዬ ¤
ያላንቺ አልኖርም እኔማ ባዶ ነኝ
እኔም እኔ አይደለሁ እማ ያንቺ እኮ ነኝ
ስጠራሽ ተነሺ
እቅፍ አድርገሽ ሳላለቅስ አባቢይኝ
እኔ ልውደቅልሽ አንቺማ አትከፊ
ይህን ክፉ ዘመን አብረሽኝ እለፊ
Comments
Post a Comment