ጭንብል😘
🔥ክፍል 3
✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
notice : እያነበባችሁት አጓጊ ቦታ ላይ ታሪኩ ቁርጥ ይልባችሁና መቼቱ ወደ ሌላ ይቀየራል እንደዚህ ሲሆንባችሁ ግራ እንዳይገባችሁ ነው ሀሳቡ አንድ ነው ማንበባችሁን ስትቀጥሉ ታገኙታላችሁ ታሪኩ ልክ እንደ አዲስ ቤት ከስር መሠረቱ ነው በእራሱ እየተገጣጠመ የሚሄደው!!
እናቱ እንዲጎርሱለት በጣቶቹ መሀል ከወሸቃት የተጠቀለለች
እንጀራ ጋር አይኑ ቢሄድም በስልኩ በሰማው የተረኝነቱ መርዶ
ምን እንደሆነ ግራ ገብቶት እያሰበ ሳለ 11 አሊያም 12 ዓመት
ያልዘለላት አንድያ ሴት ልጁ በወረቀት ተጠቅልሎ በር ላይ
ያገኘችውን ፖስታ አባቷ ከአሁን ከአሁን ይቀበለኛል ብላ
እየጠበቀች በእጆቿ ከወዲህ ወዲህ እያላወሰችው ባለችበት
ሰዓት ወደ ሶስት የሚጠጉ ሱፍ የለበሱና የታጠቁ ሰዎች
ተከታትለው ወደ ቤት ገቡ...ወጣቱ ከተቀመጠበት በድንጋጤ ተነሳ
ልጁም እያየቻቸው በፍርሀት ተንቀጠቀጠች ።
" ልብስ ደርብና ከእኛ ጋር ትሄዳለህ " አለው አንደኛው ሰውዬ
ሽጉጡን እንደደገነ።
" የማይሆነውን....ይልቁኑ በሰላም ቤቴን ልቀቁኝ " የንዴት አይሉት
የግርምት ብቻ በፂሙ የተከበበውን አፉን ከፈት አድርጎ መለሰላቸው።
"ሌላ ሀይል ከምንጠቀም በሰላም ብትሄድልን ደስ ይለን ነበር
ሆኖም ይቅርታ ግዴታ ስለሆነ ነው" በማለት አንድ መሳሪያ
የምትመስል ነገር አወጣና ተኮሰው ቲንሽዬ መርፌ ከአፈሙዙ ወጥታ አንገቱ ላይ ተሰካች..ወጣቱ በእጁ የተወጋበትን ቦታ በመያዝ ወደቀ።
🔥🔥🔥🔥
ምሽቱ ለስለስ ያለ አየር ይነፍስባታል አንዲት ወጣት ከአንድ ተለቅ
ያለ ካፌ የፅዳት ስራዋን ጨርሳ ለሀላፊው መሄድ እንደምትችል
ጠይቃ ሲፈቅድላት የጨርቅ ክብ ኮፍያ በጭንቅላቷ ላይ አጠለቀች ከግንባሯ ወደ ፀጉራ ገባ ያለውን አግድም የሚታይን ጠባሳ
ለመሸፈን ይመስላል..እቺ ልጅ በፊቷ ላይ የደስታ ምልክት
አይታይባትም እጅግ በጣም የተከፋች እንደሆነች
ታስታውቃለች..የካፌውን በር እንደወጣች በእድሜያቸው ፀና ያሉ የካፌው ጥበቃ።
" መና የኔ ልጅ ደህና እደሪልኝ " አሏት..ዘወር ብላ አየቻቸውና
አነስተኛ ብልጭ ያለች ፈገግታ አሳየቻቸው በዚህ ወቅትም
የታችኛው ከንፈሯ ከጉንጯ የተነሳው ጠባሳ ወደ ታች
ተጠልጥሏል ጥርሷን አልሸፈነውም... ለነገሩ በዚህ ቦታ ጥርስም የላትም።..ስትራመድ ከኋላ ለሚያያት ጠመም ጠመም ከማለት ባለፈ የሆነ ከእግሯ ይሁን ከወገቧ ጉዳት እንደደረሰባት
ታስታውቃለች..በአንገቷ ላይ ወፈር ያለ ሹራብ አድርጋ በእርጋታ ወደ
ቤቷ መጓዝ ጀመረች።
በሌላ አቅጣጫ አጠር ቀጠን ያለች ወደ 20 አመት የምትጠጋ
ቀይ ፀጉሮቿ እረዥም ሰልካካ አፍንጫና ስስ ቀጭን ከንፈር ፀዳ
ያሉና የተጠቀጠቁ የሚያምሩ ጥርሶች ያሏት..ጡቶቿ በጣም
ትንንሽ የሆኑ ትልቅ እንዲመስሉላት ወፈር ያለ ጡት ማስያዣ
አርጋበታለች.. የፊቷ ቅርፅ ክብ ሆኖ ትንሺዬና የሚያሳዝኑ ናቸው..ጉርድ ቀሚስ ለብሳለች እግሮቿ የሚያምሩ ናቸው። ከአንድ ሆቴል ወጥታ እስካርፕ አንገቷ ላይ አድርጋ ወደ ቤቷ መሄድ ጀመረች።...
🔥🔥🔥🔥
እናቱን እያስተመመ ካለበት በግድ እራሱን አስተውት ይዘውት የመጡትን ልጅ በፖሊስ መምሪያ ቢሮ ውስጥ በዛው ምሽት ያናግሩታል።
" ኢንስፔክተር ፍቃዱ ይቅርታ በዚህ ሁኔታ ይዘንህ በመምጣታችን" አሉት ኮማደሩ ክንዶቻቸውን ከጠረጴዛው አሰደግፈው..ከወገባቸው ጥቂቱ አጎንብሰውና ወደ ፊት ሳብ ብለው።
" ኢንስፔክተር ሳልሆን በአሁን ሰአት ስሜ ፍቃዱ ብቻ ነው
ይቅርታውም አያስፈልግም ምንም ብትሉኝ ስለማልስማማ ወደ ቤቴም ልሄ ድ ስለሆነ" አለ ፍቃዱ ፍፁም በእራስ መተማመን እየታየበት።
" በፍፁም አትሄድም ምክንያቱም እናትህ የአንተ ብቻ እናት ናቸው..ኢትዮጵያ ግን የመቶ ሚሊዮን ህዝብ እናት ነች..የአንተም፣የልጅህም የእናትህም የአያትም....... " አሉ ኮማደሩ ባሉበት ሆነው።
"እንደዚች ደልላቹሁማ አታስገቡኝም ማዐረጌን ክብሬን
ነጥቃችሁኝና አዋርዳቹሁኝ ሙሰኛ የህግ አሰከባሪ ተብዬ
ባላደረኩት ባልሰራሁት አንገቴን አስደፍታችሁ ከጎረቤት
አለያይታችሁኝ ቆይታቹሁ ዛሬ ና ግባ ትሉኛላችሁ..? አታፍሩም..? " አለ ፍቃዱ ወደ ኋላ መለስ ብሎ እያሰበ...እራሳቸው በበሉት ሙስና ጉዳዩን ፈልፍሎ ሲደርስበት የእነሱን ወንጀል ወደ እሱ አላከውበታል። ባለስልጣኖቹ ብዙ ብር ሰጥተውት ነገሩ ተደባብሶ እንዲቀር ብዙ ለምነውት አስለምነውት ሀገሬን የምሸጥ ለሆዴ የማድር ሰው
አይደለሁም በማለቱ ከስራው ተዋርዶ ክብሩን አጥቶ ነበር የተባረረው...በወቅቱ ብዙ ተጎድቷል ሞሯሉ ተሰባብሯን ግን ጠንካራ ሆኖ ያን ጊዜ አለፈው እናቱና ልጁ ከጎኑ ስላሉለት ።...
ይሄን አሁን እየተሰራ ላለው ወንጀል ከስር መሰረቱ ከተተከለበት
መሬት ፈንቅሎ ለማውጣት ከፍቃዱ ውጪ ወሳኝ መርማሪ
አይገኝም...በምንም ይሁን በምን ተብሎ የዚህን ወንጀል
ምርመራ ሂደቱን ለእሱ መስጠት ተገቢ ነው።
" አሁን የጠራንህ ማእረግህንም ክብርህንም ልናስመለስልህ ነው..እናም ግዴለም ስራውን ተቀበለን " አሉት በድጋሜ
" ውረደቴንስ..? የህሊና..የሞራል ስብራቴንስ..? " አላቸው ፍቃዱ
" ኢኒስፔክተር በቃ!!....ይሄ ልመና አይደለም የሀገር ጥሪ ነው
ወደህ ሳይሆን በግድ ትቀበላለህ እሺ!!!! " አሉ ኮማደሩ
በንዴት ከተቀመጡበት በመነሳት።
" እንቢ እንዳልኩ ብፀና መጨረሻዬ ሞት ነው አይደል ግደሉኝ..አንዴ እንደሆን ገላችሁኛል ስለዚህ ደግሜ ደጋግሜም እናገራለው እንቢ አልሠራም" አለ በንዴት በደፈረሱ አይኖቹ እያያቸው ። ኮማንደሩም
ከጭንቅላታቸው ግራና ቀኝ ቀንድ የወጣባቸው መሰላቸው በጣም
በመናደዳቸው ።..........
ይቀጥላል...
Comments
Post a Comment