ጭንብል😘
🔥ክፍል 1
✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
.
#ሁላችሁም ጀምሩት ትወዱታላችሁ😍
.
.
የመንጋቱን ብስራት አውራ ዶሮ አብስሯል ቀዝቀዛ ንፋስ ጆሮን
በጥፊ አቅልጦት ይሄዳል ቅዝቃዜው ቁርጥማት የሚያሲዘው።
ውጭ ከሚነፍሰው ቀዝቃዛ አየር ፍፁም የተለየ አየር በዚህ ክፍል
በሙቀቱ በላብ ይጠመቃሉ ነገር ግን ክፍሉ በጠቅላላ በጨለማ
ድባብ ተመቷል አንድ ማንነቱ የማይታይ ሰው ከአንድ ጠረጴዛ
አጠገብ ቆሟል ከጠረጴዛው በላይ በኩል አነስተኛ መብራት
በርታለች እናም በጠረጴዛው ላይ የተቀመጡትን እቃዎች በግልፅ
ያሳያል በአንድ ጎኑ በርከት ያለ ፎርጅድ የሆኑ ህንፃ የተሰራባቸው
ወረቀቶች ሲገኙ በሌላ በኩል መሳሪያ ( ሽጉጥ )፣ቦንብ፣ፈንጂ፣
የተለያዩ መሳሪያዎች እና ፊትን መሸፈኛ ( ጭንብል ) ፣ጓንት
የተለያዩ ነገሮች አሉ ይሄ ሰው አንድ የሚጠመድ ፈንጂ በማዘጋጀት
ላይ ነው። ከጥቂት ቆይታ በኋላ በአፍጫው የመጣውን ፈሳሽ
በእጁ ጠርጎ ወደ ላይ ሳበው በግንባሩ እየፈሰሰ ያለውንም ላብ
በልብሱ ጠረገና አንድ ስልክ አንስቶ ደወለ።
" ትሰማለህ አንተ ሰውዬ ያልኩሁን አድርግ ካልሆነ መጥፎ ነገር
ይፈፀማል ይህንን የምትወደው አይመሰለኝም" አለና ሰውዬው
ስልኩን ዘጋው በተደወለለት ሰው የወንድ ድምፅና ወፈር ያለ ነው
የሚሰማው። ደዋዩ እንደገና ደወለ።
" ፖሊሶች ናቹሁ አይደል ስሙ በቅርብ ባለ በአንድ አዲስ ድልድይ
ስር ፈንጂ አጥምጄያለው ሰው ከማለቁ በፊት በየቦታው ሰራዊትን
ላኩና ወንዞችን አስሳቹሁ አግኙ ያላቹሁ ሰአት አንድ ሰአት ብቻ ነው
መልካም እድል " በማለት ስልኩን ዘጋውና ፊት መሸፈኛውን
አድርጎ መሳሪያ በመያዝ በአንድ መሰላል ወደ ላይ ወጣ ያ ማለት
ቤቱ ከመሬት ስር ነው ያለው ማለት ነው።
አንድ በእድሜው ፀና ያለ ሰው አነስተኛ ሻንጣ በመያዝ ጥበቃዎች
ጋር ሰላም አለና ተፈትሾ ወደ ውስጥ ገባ የባንክ ደብተሩንና
ማውጣት የሚፈልገውን ብር በመፃፍ አስገባ ገንዘቡ በርካታ
ስለሆነ ወደ ውስጥ አስገብተው ሰጡት እናም ዕቃ ወደ
ሚቀመጡበት ክፍል እንዲወስዱትና እዛም የሚያወጣው እቃ
እንዳለ ተናግሮ ወደ ውስጥ ይዘውት ገቡ።
በፖሊስ መምሪያ ክፍል ውስጥ ፖሊሶች ተሰብስበው እየተነጋገሩ
ይገኛሉ የፖሊስ ሀላፊው ጠረጴዛ ከበው ለተቀመጡ የፖሊስ
አመራሮች ንግግር ያረጋሉ ።
" ትሰማላቹሁ እኔን አፍጥጦ ማየቱ ትርጉም የለውም ይሄን
ወንጀለኛ ማግኘት ተሳናቹሁ አንድ ወንጀለኛ ከእናንተ አዕምሮ በላይ
ሆነባቹሁ ድክመታችንን በግልፅ እያሳየን ነው አሁኑኑ ፍቃዱን
ካለበት ይዛቹሁልኝ እንድትመጡ ታስሮም ይሁን በእራሱ ፍቃድ
ይዛቹሁልኝ ኑ እናም........." አንድ ፖሊስ ወደ ወስጥ በመግባት
ሰላምታ ሰጠና ።
" ይቅርታ ኮማደር አዲስ ነገር ስለተፈጠረ ነው በስብሰባ መሀል
የገባሁት " አለ ተራ ወታደር
" እሺ ቀጥል ምንድን ነው አዲሱ ጉዳይ" አሉ ኮማደሩ
" የእኛ ወታደሮች ሳይደርሱበት ከተሰራ 5 ወር ያልሞላው ድልድይ
5 ሚሊየን የፈጀ በፈጂው ሙሉ ለሙሉ ዱቄት ሆኗል እስከ አሁን
አንድ ሰው ሞቷል ሌላ አንድ ባንክ በአንድ ሽማግሌ ሰው
በፎርጅድ ቡክ በርካታ ገንዘብ ተዘርፉሎ ሌላም ውድ የሆኑ
ንብረቶችም ተዘርፈዋል" በማለት እሪፖርቱን ሲያቀርብ ኮማደሩ
በንዴት ጠረጴዛውን በቦክስ ነርተውት ከተቀመጡበት
ተነሱ።.........
🔥እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ ሼር🔥
ይቀጥላል.
Comments
Post a Comment