ጭንብል
🔥ክፍል 2
✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
አንድ ወጣት ነው እድሜው በ30ዎቹ መጀመሪያ ነው ፀጉሩ ሉጫ
ነው አይኖቹ የደፈረሱ ሲጠጣ እንዳደረ ያስታውቃል ቀጠን ያለ
ሰውነት ቀይ ዳማ የቆዳ ከለር አለው ከንፈሮቹ ወፈር ያሉ ናቸው
ጥርሶቹ የፀዳ ባይሆንም ቆሻሻም አይደሉም ያማረ ቤት ውስጥ
ለብቻው ነው የሚኖረው ወደ ላጤ ነው ሴት ማለፍ ፈፅሞ
አይወድም በአጠቃላይ ለሴት ያለው ፍቅር ፍፁም የተለየ ነው ።
ለመኪና መውጫ ተብሎ የተሰራው እረጅሙ ብረት ግቢ ለእሱ
መውጫ መግቢያ አርጎታል እናም ልክ በሩን ከፍቶ ሲገባ ስልኩ
ጮሀ ስልክ ቁጥሩን አያውቀውም ግን አነሳው።
" አቤት ማን ልበል " አለ ይሀው ወጣት
" ሞትክ ነኝ " አለው በስልኩ ውስጥ የሚቆረቆረው ወፍራሙ
ድምፅ ።
" ማነ ነህ አንተ ሰውዬ እኔ ለጫዋታ ጊዜ የለኝም "
" ፐ ለካ በኔ ነው የወጣሀው "
" ሰውዬ እኔ ስልኩን ልዘጋው ነው " አለ በንዴት
" አትዘጋው አልልህም መዝጋት መፍትህ ነው ስልኩን ስትዘጋው
በዛች ቅፅፈት የህወት መንገድህ ይዘጋል " አለ ወፍራሙ ድምፅ
ጭንብሉ።
ልጁ በሰማው ነገር ደነገጠ ግራ ገባው።
" ምንድነዉ የምትለው ሰውዬ " አለ ልጁ በንዴት
" ትዘጋዋለህ ታዋራኛለህ " አለ ደዋዩ ባለ ጭንብሉ ሰው
" እሺ አናግርሀለው " አለ ፈራ ተባ እያለ
" እሺ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዛሬ እፈልጋለው " አለው
ደዋዩ ባለ ጭንብሉ
" እንዴ እየቀለድክ ነው እንዴ ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አግኝቼ
ነው የምሰጥህ " አለው ልጁ በድንጋጤ ከሰማው በኋላ።
" እኔ ልንገርህ ከምታጋጋቸው ሴቶች አንዷ ትውለድልህ ትሰማለህ
ስልክ እንድትደውል አይፈለግም እስከ ማታ 12 ድረስ ብሩ እጄ
እንዲገባ እፈልጋለው " መልሱን ሳይሰማ ስልኩን ዘጋው ። ልጁ
ደነገጠ ከግቢ እስከ ቤቱ ያለውን መንገድ እንዴት እንደተራመደ
አያስታውሰውም ሰውነቱን አላበው በተጠየቀው ገንዘብ የሆነ ሽታ
ሸቷት ወደ ላይ እንዳላት ነፍሰ ጡር ሴት አደረገው እጁ
እየተቀጠቀጠ የሚያምረውን የቪላ ቤቱን በር ቁልፍን አስገብቶ
እንዴት ይክፈተው ቁልፍን ይዞት ቀዳዳውን እየሳተ እጁ
ይንቀጠቀጣል እንደምን ከፍቶ ገባ ሶፋው ላይ አልተቀመጠም
በጀርባው ተጋደመ።
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ስልኩን አወጣ ቁጥሮችን ነካካና በቤቱ
እየተዟዟረ ሰው እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ በሞስኮቱ ወደ ውጭ
ተመልክቶ ፍፁም ሰው እንደሌለ ካረጋጉጠ በኋለ መጋረጃውን
ዘግቶ ሶፋ ላይ በሀይል ተንፍሶ ቁጭ ካለ በኋላ የነካካውን ቁጥር
ደወለ ቁና ቁና እየተነፈሰ አተነፋፈሱ አራት ጎማ ይሞላል አንድ
ጊዜ ጠራ ሁለተኛ ጠራ በዚህ ጊዜ መልእክት ገባ ከጆሮው አንስቶ
መልዕክቱን ሲያነብ ሶስተኛው እየጠራ " ሄሎ " የሚል ድምፅ ሰማ
ሀሳቡ ሁሉ መልክቱ ላይ ነበር " አንተ ሰውዬ የትም አትደውል
ብዬሀለው ወይ ስልኩን ዝጋው አሊያም ልሳንህን እኔ ልዝጋው "
የሚል መልዕክት ነበር ደንግጦ ስልኩን ዘጋው።
አንዲት አሮጊት አልጋ ከያዙ እረዥም ጊዜ እንደሆናቸው
መክሳታቸውና ምንም መቀሳቀስ አለመቻላቸው ይመሰክራል ።
ከግድግዳው ጠርዝ በአራቱም አቅጣጫ የኪዳነ ምህረት
፣የመድሀኒያለም ፣የቅ/ገብርኤል፣ የቅ /ሚካኤል ምስል ተለጠፏል
ልጃቸው ምግብ ቢያበላቸውም ምህረትን የሚሹ አይኖች በእንባ
ተሞልተው ከምስሎቹ ላይ ለወራቶች ተተክለዋል መንገዱ እንኳን
ወደ ሞት ቢሆን በአብ ቀኝ መቀመጥን የሚሹ ይመስላሉ ።
አጠገባቸው የተቀመጠው ልጃቸው ሀያዎቹን እድሜ እያገባደደ
ነው የጭንቅላቱ ፀጉር ወደ ኋላ የሸሹ ናቸው። በአፍጫውና በአፍ
ዙሪያ ችምችም ያሉ ፀጉሮች ፂም ተከቦ አፍ የት እንዳለ
አያስታውቅም ኑሮ ያልተመቸው እንደሆነ ያስታውቃል እናቱ አንድ
ጉርሻ እንዲጎርሱለት በህይወት ትንሽ እንዲቆዩለት ይለምናቸዋል
እናቱ ደጋግምው ሀኪም ቤት እንዲወስዱት ይለምኑታል እሱ በምኑ
ያሳክማቸው አቅም የለው ከማዘን ውጪ እያያቸው ወደ ሞት
ከመላክ ውጪ መፍትሄ አጥቷል።
የቤቱ በር ተንኳኳ ይሄው ወጣት እንደ ነፍሱ ከሚመለከታት
አንዲት ሴት ልጁ እያጠናች ነበረ ዘወር ብሎ በሩን እንድትከፍት
ከይቅርታ ጋር ነገራት ሄዳ ከፈተች ሰው የለም አንድ ፖስታ መሬት
ላይ አለ አነሳቺው በሩን ዘግታ ወደ አባቷ ተመለሰች ነገረቺው
ፖስታውን ሊቀበላት ሲል ለስሙ ስልክ ተባለች እንጂ ስልክ
ያልሆነች ስልክ ጥሪ አሰማች በእርግጠኝነት ከቤቱ ወጪ ቢሆን
እቺ ስልክ ስልክ ነች ብሎ ባላወጣት ነበር ግን ቤቱ ነውና
አውጥቶ ተመለከተውና ወደ ጆሮው ወሰደ።
" ደስ ይላል ተረኛ ነህ ተዘጋጅ " አለው ባለ ጭንብሉ ሰው
ለረዥም ደቂቃ ከቆየ ሳቅ በኋላ ወዲያው ስልኩን ዘጋው።
ልጁ ደንግጦ አላመነም ጭራሽ እቺ ሞባይል ጋኔን በጥፊ መቷት
እያስቀበዠራት መሰለው ግራ ተጋባ።
ቀን ላይ ብር እንዲያመጣ የተዘዘው ወጣት ከምሽቱ 12:30 ላይ
የግቢውን በር ፖሊሶች ዘለው ገቡና ከውስጥ ሆነው ላለቃቸው
ከፈቱ ግራ ቀኝ እየተመለከቱ ወደ ቤቱ ዘልቀው ገቡ ያ ብር
የተጠየቀው ወጣት አፍ ውስጥ ሽጉጥ ተቀርቅሮ ማጅራቱን ጥይቷ
በርቅሳ ወጥታ ሶፋውን በስታዋለች ወጣቱ ሞቷል ሀላፊው
ወንጀለኞቹን በማድነቅ በግርምት ሳቀ።...........
ይቀጥላል...
Comments
Post a Comment