ጭንብል😘 🔥ክፍል 3 ✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ notice : እያነበባችሁት አጓጊ ቦታ ላይ ታሪኩ ቁርጥ ይልባችሁና መቼቱ ወደ ሌላ ይቀየራል እንደዚህ ሲሆንባችሁ ግራ እንዳይገባችሁ ነው ሀሳቡ አንድ ነው ማንበባችሁን ስትቀጥሉ ታገኙታላችሁ ታሪኩ ልክ እንደ አዲስ ቤት ከስር መሠረቱ ነው በእራሱ እየተገጣጠመ የሚሄደው!! እናቱ እንዲጎርሱለት በጣቶቹ መሀል ከወሸቃት የተጠቀለለች እንጀራ ጋር አይኑ ቢሄድም በስልኩ በሰማው የተረኝነቱ መርዶ ምን እንደሆነ ግራ ገብቶት እያሰበ ሳለ 11 አሊያም 12 ዓመት ያልዘለላት አንድያ ሴት ልጁ በወረቀት ተጠቅልሎ በር ላይ ያገኘችውን ፖስታ አባቷ ከአሁን ከአሁን ይቀበለኛል ብላ እየጠበቀች በእጆቿ ከወዲህ ወዲህ እያላወሰችው ባለችበት ሰዓት ወደ ሶስት የሚጠጉ ሱፍ የለበሱና የታጠቁ ሰዎች ተከታትለው ወደ ቤት ገቡ...ወጣቱ ከተቀመጠበት በድንጋጤ ተነሳ ልጁም እያየቻቸው በፍርሀት ተንቀጠቀጠች ። " ልብስ ደርብና ከእኛ ጋር ትሄዳለህ " አለው አንደኛው ሰውዬ ሽጉጡን እንደደገነ። " የማይሆነውን....ይልቁኑ በሰላም ቤቴን ልቀቁኝ " የንዴት አይሉት የግርምት ብቻ በፂሙ የተከበበውን አፉን ከፈት አድርጎ መለሰላቸው። "ሌላ ሀይል ከምንጠቀም በሰላም ብትሄድልን ደስ ይለን ነበር ሆኖም ይቅርታ ግዴታ ስለሆነ ነው" በማለት አንድ መሳሪያ የምትመስል ነገር አወጣና ተኮሰው ቲንሽዬ መርፌ ከአፈሙዙ ወጥታ አንገቱ ላይ ተሰካች..ወጣቱ በእጁ የተወጋበትን ቦታ በመያዝ ወደቀ። 🔥🔥🔥🔥 ምሽቱ ለስለስ ያለ አየር ይነፍስባታል አንዲት ወጣት ከአንድ ተለቅ ያለ ካፌ የፅዳት ስራዋን ጨርሳ ለሀላፊው መሄድ እንደምትችል ጠይቃ ሲፈቅድላት የጨርቅ ክብ ኮፍያ በጭንቅላቷ ላይ አጠለቀች ከግንባሯ ወደ ፀጉራ ገባ ያለውን አ...