Posts

Showing posts from 2021

Get now 50 gigabytes of free internet access for all telecom networks in the Kingdom, the offer period is 24 hours only, click here now, and congratulations htt

Image
Image
 ጭንብል😘 🔥ክፍል 3 ✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ notice : እያነበባችሁት አጓጊ ቦታ ላይ ታሪኩ ቁርጥ ይልባችሁና መቼቱ ወደ ሌላ ይቀየራል እንደዚህ ሲሆንባችሁ ግራ እንዳይገባችሁ ነው ሀሳቡ አንድ ነው ማንበባችሁን ስትቀጥሉ ታገኙታላችሁ ታሪኩ ልክ እንደ አዲስ ቤት ከስር መሠረቱ ነው በእራሱ እየተገጣጠመ የሚሄደው!! እናቱ እንዲጎርሱለት በጣቶቹ መሀል ከወሸቃት የተጠቀለለች እንጀራ ጋር አይኑ ቢሄድም በስልኩ በሰማው የተረኝነቱ መርዶ ምን እንደሆነ ግራ ገብቶት እያሰበ ሳለ 11 አሊያም 12 ዓመት ያልዘለላት አንድያ ሴት ልጁ በወረቀት ተጠቅልሎ በር ላይ ያገኘችውን ፖስታ አባቷ ከአሁን ከአሁን ይቀበለኛል ብላ እየጠበቀች በእጆቿ ከወዲህ ወዲህ እያላወሰችው ባለችበት ሰዓት ወደ ሶስት የሚጠጉ ሱፍ የለበሱና የታጠቁ ሰዎች ተከታትለው ወደ ቤት ገቡ...ወጣቱ ከተቀመጠበት በድንጋጤ ተነሳ ልጁም እያየቻቸው በፍርሀት ተንቀጠቀጠች ። " ልብስ ደርብና ከእኛ ጋር ትሄዳለህ " አለው አንደኛው ሰውዬ ሽጉጡን እንደደገነ። " የማይሆነውን....ይልቁኑ በሰላም ቤቴን ልቀቁኝ " የንዴት አይሉት የግርምት ብቻ በፂሙ የተከበበውን አፉን ከፈት አድርጎ መለሰላቸው። "ሌላ ሀይል ከምንጠቀም በሰላም ብትሄድልን ደስ ይለን ነበር ሆኖም ይቅርታ ግዴታ ስለሆነ ነው" በማለት አንድ መሳሪያ የምትመስል ነገር አወጣና ተኮሰው ቲንሽዬ መርፌ ከአፈሙዙ ወጥታ አንገቱ ላይ ተሰካች..ወጣቱ በእጁ የተወጋበትን ቦታ በመያዝ ወደቀ። 🔥🔥🔥🔥 ምሽቱ ለስለስ ያለ አየር ይነፍስባታል አንዲት ወጣት ከአንድ ተለቅ ያለ ካፌ የፅዳት ስራዋን ጨርሳ ለሀላፊው መሄድ እንደምትችል ጠይቃ ሲፈቅድላት የጨርቅ ክብ ኮፍያ በጭንቅላቷ ላይ አጠለቀች ከግንባሯ ወደ ፀጉራ ገባ ያለውን አ...
Image
 ጭንብል 🔥ክፍል 2 ✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ አንድ ወጣት ነው እድሜው በ30ዎቹ መጀመሪያ ነው ፀጉሩ ሉጫ ነው አይኖቹ የደፈረሱ ሲጠጣ እንዳደረ ያስታውቃል ቀጠን ያለ ሰውነት ቀይ ዳማ የቆዳ ከለር አለው ከንፈሮቹ ወፈር ያሉ ናቸው ጥርሶቹ የፀዳ ባይሆንም ቆሻሻም አይደሉም ያማረ ቤት ውስጥ ለብቻው ነው የሚኖረው ወደ ላጤ ነው ሴት ማለፍ ፈፅሞ አይወድም በአጠቃላይ ለሴት ያለው ፍቅር ፍፁም የተለየ ነው ። ለመኪና መውጫ ተብሎ የተሰራው እረጅሙ ብረት ግቢ ለእሱ መውጫ መግቢያ አርጎታል እናም ልክ በሩን ከፍቶ ሲገባ ስልኩ ጮሀ ስልክ ቁጥሩን አያውቀውም ግን አነሳው። " አቤት ማን ልበል " አለ ይሀው ወጣት " ሞትክ ነኝ " አለው በስልኩ ውስጥ የሚቆረቆረው ወፍራሙ ድምፅ ። " ማነ ነህ አንተ ሰውዬ እኔ ለጫዋታ ጊዜ የለኝም " " ፐ ለካ በኔ ነው የወጣሀው " " ሰውዬ እኔ ስልኩን ልዘጋው ነው " አለ በንዴት " አትዘጋው አልልህም መዝጋት መፍትህ ነው ስልኩን ስትዘጋው በዛች ቅፅፈት የህወት መንገድህ ይዘጋል " አለ ወፍራሙ ድምፅ ጭንብሉ። ልጁ በሰማው ነገር ደነገጠ ግራ ገባው። " ምንድነዉ የምትለው ሰውዬ " አለ ልጁ በንዴት " ትዘጋዋለህ ታዋራኛለህ " አለ ደዋዩ ባለ ጭንብሉ ሰው " እሺ አናግርሀለው " አለ ፈራ ተባ እያለ " እሺ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዛሬ እፈልጋለው " አለው ደዋዩ ባለ ጭንብሉ " እንዴ እየቀለድክ ነው እንዴ ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አግኝቼ ነው የምሰጥህ " አለው ልጁ በድንጋጤ ከሰማው በኋላ። " እኔ ልንገርህ ከምታጋጋቸው ሴቶች አንዷ ትውለድልህ ትሰማለህ ...
Image
 ጭንብል😘 🔥ክፍል 1 ✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ . #ሁላችሁም ጀምሩት ትወዱታላችሁ😍 . . የመንጋቱን ብስራት አውራ ዶሮ አብስሯል ቀዝቀዛ ንፋስ ጆሮን በጥፊ አቅልጦት ይሄዳል ቅዝቃዜው ቁርጥማት የሚያሲዘው። ውጭ ከሚነፍሰው ቀዝቃዛ አየር ፍፁም የተለየ አየር በዚህ ክፍል በሙቀቱ በላብ ይጠመቃሉ ነገር ግን ክፍሉ በጠቅላላ በጨለማ ድባብ ተመቷል አንድ ማንነቱ የማይታይ ሰው ከአንድ ጠረጴዛ አጠገብ ቆሟል ከጠረጴዛው በላይ በኩል አነስተኛ መብራት በርታለች እናም በጠረጴዛው ላይ የተቀመጡትን እቃዎች በግልፅ ያሳያል በአንድ ጎኑ በርከት ያለ ፎርጅድ የሆኑ ህንፃ የተሰራባቸው ወረቀቶች ሲገኙ በሌላ በኩል መሳሪያ ( ሽጉጥ )፣ቦንብ፣ፈንጂ፣ የተለያዩ መሳሪያዎች እና ፊትን መሸፈኛ ( ጭንብል ) ፣ጓንት የተለያዩ ነገሮች አሉ ይሄ ሰው አንድ የሚጠመድ ፈንጂ በማዘጋጀት ላይ ነው። ከጥቂት ቆይታ በኋላ በአፍጫው የመጣውን ፈሳሽ በእጁ ጠርጎ ወደ ላይ ሳበው በግንባሩ እየፈሰሰ ያለውንም ላብ በልብሱ ጠረገና አንድ ስልክ አንስቶ ደወለ። " ትሰማለህ አንተ ሰውዬ ያልኩሁን አድርግ ካልሆነ መጥፎ ነገር ይፈፀማል ይህንን የምትወደው አይመሰለኝም" አለና ሰውዬው ስልኩን ዘጋው በተደወለለት ሰው የወንድ ድምፅና ወፈር ያለ ነው የሚሰማው። ደዋዩ እንደገና ደወለ። " ፖሊሶች ናቹሁ አይደል ስሙ በቅርብ ባለ በአንድ አዲስ ድልድይ ስር ፈንጂ አጥምጄያለው ሰው ከማለቁ በፊት በየቦታው ሰራዊትን ላኩና ወንዞችን አስሳቹሁ አግኙ ያላቹሁ ሰአት አንድ ሰአት ብቻ ነው መልካም እድል " በማለት ስልኩን ዘጋውና ፊት መሸፈኛውን አድርጎ መሳሪያ በመያዝ በአንድ መሰላል ወደ ላይ ወጣ ያ ማለት ቤቱ ከመሬት ስር ነው ያለው ማለት ነው። አንድ በእድሜው ፀና ያለ ሰው አነስተኛ ሻንጣ በመያ...
Image
        💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘              📌 #የመጨረሻው_ክፍል 📌 ...🖌እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ ታጥበው ነበር............. .........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ብሩክን አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን ለመዋጥ ስታስብ ብሩክ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ብሩኬ ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ በንዴት አን...

አትሙቺብኝ እማ

Image
ሙቺብኝ እማ═               ═══❁✿❁ ════   አትሙቺብኝ እማ  ልሙትልሽ እኔ ወገን እና ዘመድ የለኝም ከ ጎኔ ክፉሽን አልየው በ አጭሯ ዘመኔ ያላንቺማ እናቴ ህይወቴ ባዶ ነው የለኝም ጓደኛ የእኔ ነው የምለው ባክሽ አትሙቺብኝ ኑሪልኝ ዘላለም እኔነቴን የሚያውቅ ከ አንቺ ሌላ የለም ጊዜ የማይሽረው የሚኖር ዘላለም ፍቅርሽን ሚተካ በ አለም ላይም የለም          ¤ እናልሽ እማዬ ¤ ያላንቺ አልኖርም እኔማ ባዶ ነኝ እኔም እኔ አይደለሁ እማ ያንቺ እኮ ነኝ  ስጠራሽ ተነሺ  እቅፍ አድርገሽ  ሳላለቅስ አባቢይኝ እኔ ልውደቅልሽ አንቺማ አትከፊ ይህን ክፉ ዘመን አብረሽኝ እለፊ

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
       💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                  #ክፍል_3 ...🖌በክፍል ሁለት እንደምታስታውሱት መቅደስና ዮናስ ካፌ ቁጭ ብለው እያወሩ ሳለ ነበር ጌዲዮ ባጋጣሚ መጥቶ አይን ላይን የተፋጠጡት.... .......መቅደስ ከመቀመጫዋ ተነሳች ጌዲዮም በነበረበት ቆሞ እሷን እያየ ጭንቅላቱን ያዘ መቅደስ በድንጋጤ ሙክክ ብላለች እንደው አይተው ሲገምቷት ባሏ ከሌላ ወንድ ጋር የያዛትን ሴት ነው የምትመስለው ጌዲዮ ሰውነቱን እንደማንቀጥቀጥ አደረገው ይህን ጊዜ ሊያመው እንደሆነ አወቀች መቼም መቅደስ የግቢው ቅፅል ስሟ የጌዲዮ የግል ነርስ ሆኗል በፍጥነት እየተንቀጠቀጠች ቦርሳዋን ከፈተች..... ዮናስ ምንም እንዳልተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው እንኳን አላላትም ምክንያቱም ጌድዮን አይቶታል መቅደስም ቦርሳዋን ጠረንቤዛው ላይ ዘረገፈችው ይህን ጊዜ ዮናስ ብዙ ሴቶች ወደሱ እያዩ ስለነበር ሼም ያዘው ለመነሳትም አቃጣው መቅደስም በሚርበተበተው አንደበቷ ማማማ ማን ነበር ያያያ..ልከኝ...አ..ው..ዮ.ናስ.እእ..ባክህ..ክርቢት..ካካ..ለህ ይዤ ነነ.በር እ..ኮ.ጠፍኝ አለችው ዮናስም ከቦርሳዋ ከዘረገፈችው እቃ ወደ ክርቢቱ እያመለከተ ያውልሽ አላት መቅደስም ክርቢቱን ልታነሳ ስትቸኩል የብርጭቆውን ጁስ ዮናስ ላይ ደፋችበት ዮናስ በጣም ጮኸ ግን አልሰማችውም ይቅርታም ሳትለው ክርቢቱን ይዛ ወደ ጌዲዮ በረረች........ ......ከዛም ህመሙ ሳይብስበት ክርቢቱን አጫጭሳ ሰውነቱን አረጋግታ ደግፋ ከወንዶች ማደሪያ በር ላይ አድርሳው ተመለሰች ስትመለስ ዮናስም ወደማደሪያው እየሄደ ተገጣጠሙ ከዛም በጣም ይቅርታ አለችው በርግጥ በሰአቱ ስትደፋበት ብዙ ሴቶች ቢስቁም የለበሰውን...

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
 ​​​​​​​​.               💓❦የአሳዛኝ የፍቅር ታ                        #ክፍል_2 ...🖌መቅደስ ድንጋጤው ባይለቃትም አቅሟን ሰብስባ ጌድዮን ወደ ወደቀበት ስፍራ በረረች ነገር ግን በጣም እየተወራጨ ስለነበር የምታደርገው ጠፋት ከዛም አያቷ ለሚጥል በሽታ የክርቢት ጭስ ጥሩ እንደሆነ ያወሩት ትዝ አላትና ሁሉም ተማሪ ጋር እየዞረች ክብሪት ያለው ማለት ጀመረች።በሁኔታዋ እሩቅ የነበሩት ሁሉ መሰባሰብ ጀመሩ አብሮ አበድ ሳትባልም አይቀር መቅደስ በዛ ሰአት የስሟ ነገር ግድም አይሰጣትም ግን አለኝ እንቺ የሚላት አጣች ውስጥ ውስጡን ይስቁባት ይሳለቁባት ጀመር ። ከሰው እያደርኩኝ ሰው እንዴት ይናፍቀኝ ከሰው እያደርኩኝ ብርዱ እንዴት ተሰማኝ: አረ ጨከኑብኝ ተደፍቼ እያዩኝ ባላየ ባልሰማ ዝም ብለው አለፉኝ: የማን ያለህ ልበል ከንባ ጎርፍ በቀር ሰው በሰውነቱ ሲቀር ሳይከበር???? .......መቅደስ አለቀሰች እንደምንም ብላ ጭንቅላቱን ጭኖቿ ላይ አድርጋ ባፍና ባፍንጫው የሚፈልቀውን አረፋ በለበሰችው ነጠላ ትጠርግለት ጀመር አጭር ለማይባሉ ደቂቃዎች ማንቀጥቀጡ አላቆመም ነበር ከዛም ሊነቃ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሁሉም ተበተነ መቅደስ ግን አይኖቿን ከፊቱ ላይ ተክላ መንቃቱን ትጠባበቅ ጀመር። .......ከደቂቃዎችም ቡሀላ ጌድዮ አይኖቹ ከመቅደስ አይኖች ጋር ተጋጭተው ተገለጡ የመቅደስ አይኖች ማልቀሷን ያሳብቃሉ ከንፈሮቿም ይንቀጠቀጣሉ ጉንጮቿ በንባ እርሰው ላይን ያሳሳሉ ጌዲዮ ትኩር ብሎ አያት እሷም ከመደንገጧ የተነሳ ሰውነቷን መቆጣጠር ከበዳት። ጌዲዮ ቀስ ብሎ ከግሮቿ ላይ ተነሳ አስተያየቱ...

💓❦የልቤ ትርታ❦💓

Image
 ​​​​​​​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_1 ...🖌ዛሬ ቀኑ አዲስ ነው አሮጌ አመት አልቆ ሁሉም አዲስ ሆኗል ትምህርት ቤቶችም እየተከፈቱ ነው። ዩንቨርስቲዎችም ለተማሪዎቻቸው አቀባበል እያደረጉ ነው። ጌዲዮ የሁለተኛ አመት አመት የዲግሪ ተማሪ ነው። በባለፈው አመት አገር አቀፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጣውም እሱ ነው.....ዛሬ የሁለተኛ አመቱን ትምርት ሊቀጥል ሻንጣውን ሸክፎ የጅማ ዩኒቨርሲቲን እረግጧል።እናም አቀርቅሮ በመንገድ ላይ ሳለ አንዲት ቅልብልብ ያለች ቆንጆ ፊትለፊቱ መጥታ ተጋጩ ከዚያም እያየህ አትሄድም ብላ ጮኸችበት እሱ ግን ምንም ሳይላት መንገዱን ቀጠለ ልጅቱም ይቅርትታ ባለመጠየቁ ተናዳ ተከትላ ሄዳ ልብሱን ያዘችና እያናገርኩህ አይደል አለችው ያምሀል አታስተውልም እያለች....የስድብ አይነት ታወርድበት ጀመር ጌዲዮን ግን እንኳን ይቅርታ ሊጠይቃት ቀናም አላለላት...... ብዙ ተማሪዎች ከሩቅ ሆነው በፍርሀት ነበር የሚያዩዋቸው ምክንያቱም ጌዲዮ ከባድ የሚጥል በሽታ አለበት ጊቢውን ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ከመፅሀፍና ደብተሩ ውጪ ጓደኛው ነኝ የሚል ማንም የለም ሲበዛ ኮስታራ ዝምተኛ። ብቸኛ ነው ከትምህርቱ ውጪ ከመምህራኖቹ ጋር እንኳን አፍ ለአፍ ገጥሞ አያውቅም ማንም ሲስቅ አይቼዋለሁ የሚል የለም ከላይ ጀምሮ እስከታች ሁሉም ይፈሩታል። መቅደስ ግን አታውቀውም የመጀመሪያ አመት ትምህርቷን ለመከታተል ገና ጊቢውን መርገጧ ነው!!! .........

ውዴ

 ═══❁🌺✿🌺❁ ══════ እቅር ብዬሸለው ══════❁✿❁ ══════  ያለ ምንም ጥፋት ይቅርታ ጠየቅሽኝ ግፍ ሳትፈፅሚብኝ በፍቅር አሸነፍሽኝ በክህደት ቃሌ  ሰጠሽኝ ምሳሌ በቃ ተሸነፍሁኝ እጄንም አነሳሁ  ይቅርታሽ ማረኸኝ እኔነቴን አጣሁ በደሌ ሳያንስሽ በእምነትሽ ተቀጣሁ ይቅር በይኝ እህቴ ለሰራሁት ጥፋት ፍቅርሽን ገፍቼ ለሄድሁባት ሰአት በጣም ፀፅቶኛል ጥፋቴን ላርማት ያችን ቀን ላልደግማት ይቅሮታሽን ስጭኝ ሀቁን ልናገራት